Web Content Display Web Content Display

 

ማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊዩል ኮርፓሬሽን

የኢትዮጵያ ማዕድን፣ ነዳጅና የባዮፊዩል ኮርፖሬሽን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 367/2008 ከታህሳስ 2008 ዓ.ም  ጀምሮ  በተፈቀደ ካፒታል ብር 15,267,000,000 እና በተከፈለ ካፒታል ብር 4,017,000,000 በመንግስት የልማት ድርጅትነት የተቋቋመ ሲሆን የቀድሞዎቹን የኢትዮጵያ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ልማት ድርጅት እና የኢትዮጵያ የማዕድን ልማት አክሲዮን ማህበርን ሕጋዊ ሰውነት በማፍረስ እንዲሁም የባዮፊዩል ልማትን በኮርፖሬሽኑ በማካተት እንዲደራጅ ተድርጓል፡፡

 

የኮርፓሬሽኑ ተልዕኮ፡-

ኢኮኖሚያዊና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ማዕድናት፣ ነዳጅና ባዮፊዩል ሃብቶችን በመፈለግ በማጥናት በማልማትና ለገበያ በማቅረብ  እንዲሁም ከዘርፉ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አገልግሎቶችን በመስጠት  ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪ ተቋም በመፍጠር አገራዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ

የኮርፓሬሽኑ ራዕይ፡-

በ2020 በዓለም ገበያ ተመራጭነት ያለው ማዕድን፣ነዳጅና ባዮፊዩል ምርትና አገልግሎት በማቅረብ ግንባር ቀደም የአገር ኢኮኖሚ አለኝታ መሆን፡፡

ኮርፓሬሽኑ የተቋቋመት ዓላማ፡-

  • በማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊዩል ሥራዎች ውስጥ በቀጥታ በመሳተፍ የአገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት በተገቢው ሁኔታ ማልማት፤
  • በዘርፋ የአገር በቀል አቅምን በመገንባት በዘርፋ ለሚሰማሩ ሌሎች እገዛ ማድረግና ከዘርፋ የአገሪቱን ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፤
  • ከስትራቴጂካዊ አስፈላጊነታቸው አንፃር ከፍተኛ ግምት በሚሰጣቸውና በግሉ ዘርፍ ሊሟሉ በማይችሉ ዘርፎች ላይ በመሳተፍ ክፍተቶችን መሙላት፤
  • ተወዳዳሪ የመንግስት የልምት ድርጅቶች በመሆን በአገሪቱ ኢኮኖሚ ግንባታ እገዛ ማድረግ፡፡
  • ራሱ ወይም እንደሁኔታው ከሌሎች ጋር በመሆን በማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊዩል ሥራዎች ኢንቨስትሜት ላይ መሳተፍ፣ ማልማትና ማምረት፤
  • ከዘርፍ ጋር የተያያዙ የማማከር፣ የድሪሊንግ፣ የላብራቶሪ፣ መረጃ የመሰብስብ፣ መተንተንና የመተርጎም፣ የአዋጭነት ጥናት ሥራዎች መስራት፣ ስልጠናና መሳሰሉ አገልግሎቶችን መስጠት እና
  •  በአገር ውስጥና በውጭ አገራት ተወዳዳሪና አትራፊ ሆኖ እንዲቀሳቀስ እገዛ የሚያርጉለትን ፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂና የዘመናዊ አስተዳደር ግብዓቶችን ለማግኘት የሚያስችለውን ጥናት ማካሄድ፣ የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብና ሲፈቀድ ተግባራዊ ማድረግ ናቸው፡፡

ኮርፖሬሽኑ የሰው ኃይል፡- ወንድ 776 ፣ ሴት 266 ድምር 1,042

የደርጅቱ ዋና ዋና  ምርቶች፡-  የታንታለም፣ ካኦሊን፣  ዶሎማይትና ሌሎች የኢንዱስትሪ ማዕድናት እንዲሁም ጨው፣  ባዮፊውልና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት፡- በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሃያ ሁለት ማዞሪያ አካባቢ ነው፡፡

የድርጅቱ ቅርንጫፍ የማምረቻ ቦታዎች የሚገኙበት ቦታ፡- በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሻኪሶና   ቀንጢቻ በተባሉት ሥፍራዎች ነው፡፡