የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2012 በጀት ዓመት ብር 122.14 ቢሊዮን ገቢ አገኘ::
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብር 649.65ሚሊዮን አተረፈ
በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በማኑፋክቸሪነግ ዘርፍ የተሰማሩ አምስት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 174 ሚሊዮን አተረፉ
በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በንግድና አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ አራት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 77.6ሚሊዮን አተረፉ
በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ብር 52.3 ቢሊዮን አተረፉ
Back

የኤጀንሲው አመራሮች የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

 

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረመስቀል፣ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካል እና ሌሎች የኤጀንሲው ሥራአመራር አባላትን ያካተተ የኤጀንሲው አመራር ታህሳስ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በሞጆ እና ቢሾፍቱ ከተሞች ተገኝቶ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት(ኢባትሎአድ) የሥራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡ ከሞጆ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ መሠረት አሰፋ ጋርም በጋራ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡

አመራሮቹ በቅድሚያ የጎበኙት በሞጆ ከተማ የሚገኘውን የድርጅቱን ደረቅ ወደብ አገልግሎት ነው፡፡ የድረጀጅቱ ዋና ሥራአስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳና የወደቡ የሥራ ኃላፊዎች በወደቡ የሚገኙ መጋዘኖችን፣በክምችት የሚገኙ ኮንቴይነሮችን፣ልዩ ልዩ መገልገያ ማሽኖችን፣በመገንባት ላይ ያሉ ጋራዥና ሕንጻ ለአመራሮቹ አስጎብኝተዋል፤ ገለጻም አድርገዋል፡፡

ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት አኳያ የወደቡ አገልግሎት ፍላጎት እየሰፋ መጥቷል፡፡ ከዚህ አንጻር የወደቡን አቅም ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ ለዚህ ደግሞ ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ያለው 43 ሄክታር ያህል የመሬት ይዞታ በቂ ስለማይሆን ተጨማሪ 30 ሄክታር የሚሆን መሬት ከከተማ አስተዳደሩ ተጠይቆ በሂደት ላይ ይገናል፡፡ ይኸው የመሬት አቅርቦት ተፋጥኖ ወደ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ትግበራ ለመግባት እንዲቻል የኤጀንሲው አመራሮችና የድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች ሞጆ ከተማ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ተገኝተው ከከንቲባዋ ከወ/ሮ መሠረት አሰፋ ጋር በጉዳዩ ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚህም ወቅት የከተማዋ ከንቲባ ድርጅቱ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ከሚያደርገው አስተዋጽኦ ጎን ለጎን ለከተማው ኅብረተሰብ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ኑሮ መሻሻል የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የከተማው መስተዳድርም የቀረበለትን የመሬት ጥያቄ ከሀገሪቱና ከአካባቢው የመልማት ፍላጎት አንጻር አይቶ ድርጅቱ በጠየቀው መሬት ላይ ያሉ አርሶአደሮችን በሌላ ሥፍራ በአግባቡ በማስፈር ምላሽ እንደሚሰጥ ቃል ገብተው፣ለዚህም የከተማውን የአቅም ውስንነት ተረድተው የኦሮሚያ ክልል እና የኤጀንሲው ድጋፍ እንደሚያሻው አስረድተው ውይይቱ በመግባባት ተቋጭቷል፡፡
ከሰዓት በኋላ ባለው ጊዜ አመራሮቹ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘውን የበቦ ጋያ የማሪታይምና ሎጀስቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል የጎበኙ ሲሆን፣በጉብኝቱ ማጠቃለያ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረመስቀል ድርጅቱ ወጪና ገቢ ዕቃዎችን በማስተናገድ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ አገልግሎቱን እያደገ ከመጣው ፍላጎት አንጻር ለማስፋፋት ኤጀንሲው የሚጠበቅበትን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸው የዕለቱ መርሐግብር ተጠናቋል፡፡


  ክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል

 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

Web Content Display Web Content Display

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል መልዕክት

 

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 1097/2011  መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን እንደገና እንዲዋቀሩ ማድረጉን ተከትሎ በደንብ ቁጥር 445/2011 ተቋቁሟል፡፡ ኤጀንሲው ከቀድሞው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በተለየ መልኩ አዲስ ተልዕኮ ፣ የትኩረት መስክ እና አደረጃጀት እንዲይዝ ተደርጓል፡፡ 

አዲሱን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት ተከትሎ የተቋቋመውን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲን  በዋና ዳይሬክተርነት እንድመራ ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቶኛል፡፡ ኤጀንሲው በሥሩ 22 ተጠሪ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አሉት፡፡

ኤጀንሲው  የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውጤታማ ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና የኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓት ዝርጋታ ፣ አመራርና አስተዳደር ክትትል ፣በመንግሥት የልማት ድርጅቶችና አክሲዮን ማህበራት ውስጥ መንግሥት ያለውን የባለቤትነት መብት ማስጠበቅ ፣በመንግሥት ልማት ፖሊሲ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስምሪት መካከል የሚኖረውን ቅንጅት ማሳለጥ እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር  የመንግሥት የባለቤትነት ፣ የተቆጣጣሪ እና ፖሊሲ አውጪውን አካላት ኃላፊነትና ሚና በለየ መልኩ መተግበሩን ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ ዋና ዋና ዓላማዎችን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ሌሎች ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶችም በመቋቋሚያ ደንቡ ተገልፀዋል፡፡

ኤጀንሲው እነዚህን ዓላማዎች እና  ኃላፊነቶች ለማሳካትም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መልኩ ትርፋማነት ላይ አተኩረው እንዲሰሩ በማስቻል በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ማድረግ እና የሀገርን ኢኮኖሚ መደገፍ እንዲችሉ ማብቃት ይጠበቅበታል፡፡

የኤጀንሲው ፣ የተጠሪ የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ፈጻሚዎች ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት  ለመወጣት የመላው የሀገራችን ህዝብ እና የደንበኛና የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ድጋፍ ወሳኝ እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን፡፡

በመሆኑም በምንከተለው ግልጽ አሰራር መሰረት የደንበኛና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ድጋፍ እንደምናበረታታ እያስታወቅን፣ ለጋራ ዓላማችን ስኬት ለምታደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ክብር እንዳለን እና ትኩረት ሰጥተን ሁልጊዜም ለመሻሻል እንደምንሰራ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

Web Content Display Web Content Display