የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2012 በጀት ዓመት ብር 122.14 ቢሊዮን ገቢ አገኘ::
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብር 649.65ሚሊዮን አተረፈ
በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በማኑፋክቸሪነግ ዘርፍ የተሰማሩ አምስት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 174 ሚሊዮን አተረፉ
በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በንግድና አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ አራት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 77.6ሚሊዮን አተረፉ
በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ብር 52.3 ቢሊዮን አተረፉ
Back

በግብርና እና አግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ሁለት ኮርፖሬሽኖች የግማሽ በጀት ዓመት አፈጻጸም ተገመገመ

 

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ስር ያሉና በግብርና እና አግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች እና የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽኖች የ2012 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የኤጀንሲው አመራሮች፣የየኮርፖሬሽኖቹ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችና የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት መድረክ የካቲት 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በኤጀንሲው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተገመገመ፡፡

በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሽን አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን፣የግምገማውን መድረክ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረ መስቀል መርተውታል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ሪፖርት ቁልፍ የሪፎርም ሥራዎች እና አበይት የኦፕሬሽን አፈጻጸሞች በሚሉ ምድቦች የተጠቃለለ ነው፡፡ በቁልፍ የሪፎርም ሥራዎች ኮርፖሬሽኑ አቅዶ ያከናወናቸው የአደረጃጀትና የአሠራር ሂደትን ቀጣይነት ባለው መልኩ የማሻሻል፣የለውጥ መሣሪያዎችን በተደራጀ መልኩ የመተግበር፣የመረጃ ሥራ አመራር ሥርዓት (MIS) የመዘርጋት፣የሰው ሀብት አቅም ማጎልበት፣የሥራ መመሪያዎችን መቅረጽና በሥራ ላይ የማዋል እና ከሥርዓተ ጾታ፣ ከአካል ጉዳተኝነት፣ ከኤች አይ ቪ ኤድስ ከአካባቢ ጥበቃና የኮፖሬት ማኅበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት ጋር የተያያዙ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ናቸው፡፡ አፈጻጸማቸውም በጥሩ ደረጃ እንደሆነ በግምገማው ታይቷል፡፡

በኦፕሬሽን ግቦች አፈጻጸም ኮርፖሬሽኑ ከግብርና ግብዓት አቅርቦት፣ከምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች፣ከእርሻ መሳሪያ ሽያጭ፣ከሜካናይዜ አገልግሎትና ኢንጂነሪንግ እንዲሁም ከተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት በድምሩ ብር 878 ሚሊዮን ገቢ በግማሽ ዓመት ለማግኘት አቅዶ ብር 863.9 ሚሊዮን በማግኘቱ የዕቅዱን 98 በመቶ አሳክቷል፡፡ኮርፖሬሽኑ በግማሽ ዓመቱ የብር 5.2 ሚሊዮን ኪሳራ እንደሚደርስበት አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ወጪውን በከፍተኛ መጠን መቆጠብ በመቻሉ ብር 41.4 ሚሊዮን አትርፏል፡፡

በግምገማው ወቅት ኮርፖሬሽኑ የለውጥ ሥራዎችን በባለቤትነት ይዞ በማስኬድ፣ችግሮችን ለይቶ በውስጥ አቅም ለመፍታት የተደረገው ጥረት፣ሂሳብን በወቅቱ ዘግቶ በማስመርመር፣ማኅበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት እንዲሁም ገቢና ትርፉን ለማሳደግ የተደረጉ ጥረቶችና የተገኙ ውጤቶች አበረታች መሆናቸው ተገልጿል፡፡ በቀጣዩ የበጀት ዓመቱ ወራትም ወደኋላ የቀሩ ተግባራት ላይ በማተኮር እነዚሁ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማሳሰቢያ ተሰጥቶ ግምገማው ተጠናቋል፡፡

ከሰዓት በኋላ በኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር በአቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል መድረክ መሪነት የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ተገምግሟል፡፡ በቀረበው ሪፖርት እንደተገለጸው ኮርፖሬሽኑ በግማሽ ዓመቱ 89,598.8 ቶን ስኳር ለማምረት አቅዶ 62,339.9 ቶን ማምረት በመቻሉ የዕቅዱን 70 በመቶ አከናውኗል፡፡ የኢታኖል ምርትን በተመለከተ በዚሁ ጊዜ ውስጥ 5,365.9 ሜ.ኩ. ኢታኖል ለማምረት አቅዶ 2,536.52 ሜ.ኩ. ወይም የዕቅዱን 47.27 በመቶ አምርቷል፡፡

በምርት ሽያጭ ገቢ ረገድ ኮርፖሬሽኑ በግማሽ ዓመቱ ከስኳር ብር 6.4 ቢሊዮን ለማግኘት አቅዶ ብር 5.2 ቢሊዮን ወይም የዕቅዱን 81 በመቶ ገቢ አግኝቷል፡፡ ከኢታኖል ብር 187.3 ሚሊዮን ለማግኘት ታቅዶ ብር 44.5 ሚሊዮን የተገኘ ሲሆን፣ ከሞላሰስ 93.2 ሚሊዮን ታቅዶ 15.6 ሚሊዮን ሊገኝ ችሏል፡፡ በአጠቃላይ ኮርፖሬሽኑ በግማሽ ዓመቱ ብር 6.6 ቢሊዮን የሽያጭ ገቢ አቅዶ ብር 5.2 ቢሊዮን ወይም የዕቅዱን 78 በመቶ ማግኘት መቻሉ በግምገማው ወቅት ተገልጿል፡፡

በግምገማው መጨረሻም የኮርፖሬሽኑ አፈጻጸም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በክረምት ወራት በራስ አቅም ያከናወናቸው የጥገና ተግባራት፣አደረጃጀቱን ለማስተካከል የሄደበት መንገድ፣የሰው ኃይል አቅሙን ለማሳደግ ያደረገው ጥረት፣ወጪውን ለመቀነስ የተከተለው ስትራቴጂና ያገኘው ውጤት የሚበረታታ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በቀጣይ በሪፎርም ሥራዎች፣ከፕሮጀክት ጋር የተያያዙ ችግሮችን በመፍታት፣ሂሳብ መዝጋትና በውጭ ኦዲተር በማስመርመር፣ የስጋት አስተዳደርና እንዲሁም የኮርፖሬት አስተዳደርን ሥራ ላይ ማዋል ላይ ኮርፖሬሽኑ ትኩረት አድርጎ እንዲሠራ አቅጣጫ ተሰጥቶ የዕለቱ ግምገማ ተጠቃሏል፡፡


  ክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል

 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

Web Content Display Web Content Display

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል መልዕክት

 

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 1097/2011  መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን እንደገና እንዲዋቀሩ ማድረጉን ተከትሎ በደንብ ቁጥር 445/2011 ተቋቁሟል፡፡ ኤጀንሲው ከቀድሞው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በተለየ መልኩ አዲስ ተልዕኮ ፣ የትኩረት መስክ እና አደረጃጀት እንዲይዝ ተደርጓል፡፡ 

አዲሱን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት ተከትሎ የተቋቋመውን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲን  በዋና ዳይሬክተርነት እንድመራ ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቶኛል፡፡ ኤጀንሲው በሥሩ 22 ተጠሪ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አሉት፡፡

ኤጀንሲው  የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውጤታማ ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና የኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓት ዝርጋታ ፣ አመራርና አስተዳደር ክትትል ፣በመንግሥት የልማት ድርጅቶችና አክሲዮን ማህበራት ውስጥ መንግሥት ያለውን የባለቤትነት መብት ማስጠበቅ ፣በመንግሥት ልማት ፖሊሲ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስምሪት መካከል የሚኖረውን ቅንጅት ማሳለጥ እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር  የመንግሥት የባለቤትነት ፣ የተቆጣጣሪ እና ፖሊሲ አውጪውን አካላት ኃላፊነትና ሚና በለየ መልኩ መተግበሩን ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ ዋና ዋና ዓላማዎችን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ሌሎች ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶችም በመቋቋሚያ ደንቡ ተገልፀዋል፡፡

ኤጀንሲው እነዚህን ዓላማዎች እና  ኃላፊነቶች ለማሳካትም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መልኩ ትርፋማነት ላይ አተኩረው እንዲሰሩ በማስቻል በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ማድረግ እና የሀገርን ኢኮኖሚ መደገፍ እንዲችሉ ማብቃት ይጠበቅበታል፡፡

የኤጀንሲው ፣ የተጠሪ የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ፈጻሚዎች ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት  ለመወጣት የመላው የሀገራችን ህዝብ እና የደንበኛና የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ድጋፍ ወሳኝ እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን፡፡

በመሆኑም በምንከተለው ግልጽ አሰራር መሰረት የደንበኛና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ድጋፍ እንደምናበረታታ እያስታወቅን፣ ለጋራ ዓላማችን ስኬት ለምታደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ክብር እንዳለን እና ትኩረት ሰጥተን ሁልጊዜም ለመሻሻል እንደምንሰራ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

Web Content Display Web Content Display