የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብር 649.65 ሚሊዮን አተረፈ
በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በማኑፋክቸሪነግ ዘርፍ የተሰማሩ አምስት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 174 ሚሊዮን አተረፉ
የስኳር ኮርፖሬሽን የ2011 ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2012 ዕቅድ ዝግጅት ተገመገመ
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከታክስ በፊት ብር 1.71 ቢሊዮን አተረፈ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ብር 324 ሚሊዮን አተረፈ
Back

የኢትዮጵያ ግብርና እና የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽኖች በ2011 በጀት ዓመት ብር 112.2 ሚሊዮን አተረፉ

 

 

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ሥር የሚገኙ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ብር 96.1 ሚሊዮን እና የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ብር15.1 ሚሊዮን በድምሩ  ብር112.2 ሚሊዮን በ2011 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት አተረፉ፡፡

ይህ የታወቀው የኮርፖሬሽኖቹ የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት በኤጀንሲው መሰብሰቢያ አዳራሽ ነሐሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም. በተገመገመበት ወቅት ኮርፖሬሽኖቹ ካቀረቧቸው ሪፖርቶች ነው፡፡

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ምርት ማሳደጊያ አቅርቦት፣ የምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች ምርትና ሽያጭ፣የሜካናይዜሽን እና ኢንጂነሪንግ አገልግሎት፣የእርሻ መሣሪያ እና የለዋወጫ ዕቃ አቅርቦት ፣የተሸከርካሪና የጥገና በተሰኙ የአገልግሎት ዘርፎች ተደራጅቶ በዋነኛነት ለግብርናው ዘርፍ ግብዓት የሚውሉ ማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘር፣ ማሽነሪዎች እና መለዋወጫዎች ያቀርባል፡፡ የሜካናይዜሽን አገልግሎትእና የተሸከርካሪዎች ጥገና ይሰጣል፡፡ የዱር ሙጫና ዕጣን ደግሞ ወደ ውጭ ገበያ ይልካል፡፡ ከእነዚህ ተግባራቱ በበጀት ዓመቱ ብር 3.3 ቢሊዮን ገቢ ለማግኘት አቅዶ ብር 2.2 ቢሊዮን በማግኘት ዕቅዱን በ68% አሳክቷል፡፡ በትርፍ ረገድ ብር111.6 ሚሊዮን ከታክስ በፊት ለማትረፍ አቅዶ ብር 96.1ሚሊዮን በማትረፉ የዕቅዱን 86% አከናውኗል፡፡ ከኤክስፖርት ደግሞ 3.7 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዶ 1.1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በማግኘት የዕቅዱን 29% አሳክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለተጠቃሚዎች መሠረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በማቅረብ፣ የግዥ አገልግሎት እና የማማከር ተግባር በማከናወን፣ ቡና፣ የቅባት እህል፣ ጥራጥሬ እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬ ለውጭ ገበያ በመላክ ተግባራት የተሰማራ ነው፡፡ በእነዚህ ሥራዎች በበጀት ዓመቱ ብር 9.12 ቢሊዮን ከሀገር ውስጥና የውጭ ገበያ ሽያጭ ገቢ በማግኘት ብር 31.4 ሚሊዮን  ለማትረፍ አቅዶ ብር 5.66 ቢሊዮን የሽያጭ ገቢ አግኝቷል፡፡ ይህም የዕቅዱን 62% ማሳካቱን ያሳያል፡፡በትርፍ ረገድ ብር 15.12 ሚሊዮን ማትረፍ በመቻሉ የዕቅዱን 48.15% አከናውኖ ቀደም ባሉ ተከታታይ ዓመታት ከነበረበት ኪሣራ የወጣ መሆኑ በግምገማው ወቅት ተገልዷል፡፡

የግምገማ መድረኩን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረመስቀል እና የኦኘሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታው ኃ/ሚካኤል የመሩት ሲሆን፣ የየኮርፖሬሽኖቹ የቦርድ ተወካዮች፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የኤጀንሲው የግብርና እና የንግድ ዳይሬክቶሬቶች ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡


  ክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል

 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

Web Content Display Web Content Display

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል መልዕክት

 

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 1097/2011  መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን እንደገና እንዲዋቀሩ ማድረጉን ተከትሎ በደንብ ቁጥር 445/2011 ተቋቁሟል፡፡ ኤጀንሲው ከቀድሞው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በተለየ መልኩ አዲስ ተልዕኮ ፣ የትኩረት መስክ እና አደረጃጀት እንዲይዝ ተደርጓል፡፡ 

አዲሱን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት ተከትሎ የተቋቋመውን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲን  በዋና ዳይሬክተርነት እንድመራ ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቶኛል፡፡ ኤጀንሲው በሥሩ 22 ተጠሪ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አሉት፡፡

ኤጀንሲው  የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውጤታማ ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና የኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓት ዝርጋታ ፣ አመራርና አስተዳደር ክትትል ፣በመንግሥት የልማት ድርጅቶችና አክሲዮን ማህበራት ውስጥ መንግሥት ያለውን የባለቤትነት መብት ማስጠበቅ ፣በመንግሥት ልማት ፖሊሲ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስምሪት መካከል የሚኖረውን ቅንጅት ማሳለጥ እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር  የመንግሥት የባለቤትነት ፣ የተቆጣጣሪ እና ፖሊሲ አውጪውን አካላት ኃላፊነትና ሚና በለየ መልኩ መተግበሩን ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ ዋና ዋና ዓላማዎችን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ሌሎች ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶችም በመቋቋሚያ ደንቡ ተገልፀዋል፡፡

ኤጀንሲው እነዚህን ዓላማዎች እና  ኃላፊነቶች ለማሳካትም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መልኩ ትርፋማነት ላይ አተኩረው እንዲሰሩ በማስቻል በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ማድረግ እና የሀገርን ኢኮኖሚ መደገፍ እንዲችሉ ማብቃት ይጠበቅበታል፡፡

የኤጀንሲው ፣ የተጠሪ የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ፈጻሚዎች ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት  ለመወጣት የመላው የሀገራችን ህዝብ እና የደንበኛና የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ድጋፍ ወሳኝ እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን፡፡

በመሆኑም በምንከተለው ግልጽ አሰራር መሰረት የደንበኛና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ድጋፍ እንደምናበረታታ እያስታወቅን፣ ለጋራ ዓላማችን ስኬት ለምታደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ክብር እንዳለን እና ትኩረት ሰጥተን ሁልጊዜም ለመሻሻል እንደምንሰራ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

Web Content Display Web Content Display