የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብር 649.65 ሚሊዮን አተረፈ
በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በማኑፋክቸሪነግ ዘርፍ የተሰማሩ አምስት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 174 ሚሊዮን አተረፉ
የስኳር ኮርፖሬሽን የ2011 ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2012 ዕቅድ ዝግጅት ተገመገመ
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከታክስ በፊት ብር 1.71 ቢሊዮን አተረፈ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ብር 324 ሚሊዮን አተረፈ
Back

የስኳር ኮርፖሬሽን የ2011 ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2012 ዕቅድ ዝግጅት ተገመገመ

 

የስኳር ኮርፖሬሽን የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት መስከረም 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ ስብሰባ ተገመገመ፡፡ የግምገማ መድረኩን የመሩት የኤጀንሲው የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል ሲሆኑ፣ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራአስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከኤጀንሲው የግብርናና አግሮኢንዱስትሪ ዳይሬክተርና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

በግምገማው ላይ እንደተገለጸው ኮርፖሬሽኑ በሶስቱ ነባር ፋብሪካዎች ማለትም በወንጂ፣መተሐራ እና ፊንጫ እንዲሁም በአዳዲሶቹ  ተንዳሆ፣ከሰም፣አርጆ ዴዴሳ፣ኩራዝ ቁጥር ሁለትና ሶስት በድምሩ በአምስት ፋብሪካዎች 419, 415 ቶን ስኳር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለማምረት አቅዶ 251,635 ቶን በማምረት የዕቅዱን 60 በመቶ አከናውኗል፡፡  በሌላ በኩል በአገዳ እርሻ ኦፕሬሽን ዘርፍ 9,938 ሄክታር የአገዳ ተከላ ለማከናወን አቅዶ 8,343 ሄክታር በመትከሉ የዕቅዱን 84 በመቶ ማከናወን ችሏል፡፡ በ2012 በጀት ዓመት ዕቅዱ የስኳር ምርቱን ወደ 483,609 ቶን  እና የአገዳ ተከላውን ወደ 10,500 ሄክታር ለማሳደግ ግብ ይዟል፡፡

በግምገማው ማጠቃለያ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል ኮርፖሬሽኑ የገጠሙትን ችግሮች ተቋቁሞ በ2011 በጀት ዓመት ያከናወናቸው ተግባራት ተስፋ ሰጪ በመሆናቸው ሊበረታታ እንደሚገባ ገልጸው፣ በ2012 በጀት ዓመት የየያዛቸው ግቦች ኮርፖሬሽኑ  በለውጥ ምዕራፍ ውስጥ መሆኑን የሚያሳዩ ስለሆኑ  አመራሩና መላው ሠራተኛ የኮርፖሬሽኑን ሀብት ከብክነት በጸዳ መንገድ በአግባቡ ሥራ ላይ አውሎ የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ ጠንክሮ እንዲሰራ አስገንዝበዋል፡፡ 


  ክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል

 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

Web Content Display Web Content Display

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል መልዕክት

 

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 1097/2011  መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን እንደገና እንዲዋቀሩ ማድረጉን ተከትሎ በደንብ ቁጥር 445/2011 ተቋቁሟል፡፡ ኤጀንሲው ከቀድሞው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በተለየ መልኩ አዲስ ተልዕኮ ፣ የትኩረት መስክ እና አደረጃጀት እንዲይዝ ተደርጓል፡፡ 

አዲሱን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት ተከትሎ የተቋቋመውን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲን  በዋና ዳይሬክተርነት እንድመራ ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቶኛል፡፡ ኤጀንሲው በሥሩ 22 ተጠሪ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አሉት፡፡

ኤጀንሲው  የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውጤታማ ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና የኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓት ዝርጋታ ፣ አመራርና አስተዳደር ክትትል ፣በመንግሥት የልማት ድርጅቶችና አክሲዮን ማህበራት ውስጥ መንግሥት ያለውን የባለቤትነት መብት ማስጠበቅ ፣በመንግሥት ልማት ፖሊሲ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስምሪት መካከል የሚኖረውን ቅንጅት ማሳለጥ እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር  የመንግሥት የባለቤትነት ፣ የተቆጣጣሪ እና ፖሊሲ አውጪውን አካላት ኃላፊነትና ሚና በለየ መልኩ መተግበሩን ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ ዋና ዋና ዓላማዎችን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ሌሎች ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶችም በመቋቋሚያ ደንቡ ተገልፀዋል፡፡

ኤጀንሲው እነዚህን ዓላማዎች እና  ኃላፊነቶች ለማሳካትም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መልኩ ትርፋማነት ላይ አተኩረው እንዲሰሩ በማስቻል በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ማድረግ እና የሀገርን ኢኮኖሚ መደገፍ እንዲችሉ ማብቃት ይጠበቅበታል፡፡

የኤጀንሲው ፣ የተጠሪ የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ፈጻሚዎች ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት  ለመወጣት የመላው የሀገራችን ህዝብ እና የደንበኛና የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ድጋፍ ወሳኝ እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን፡፡

በመሆኑም በምንከተለው ግልጽ አሰራር መሰረት የደንበኛና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ድጋፍ እንደምናበረታታ እያስታወቅን፣ ለጋራ ዓላማችን ስኬት ለምታደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ክብር እንዳለን እና ትኩረት ሰጥተን ሁልጊዜም ለመሻሻል እንደምንሰራ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

Web Content Display Web Content Display