የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2012 በጀት ዓመት ብር 122.14 ቢሊዮን ገቢ አገኘ::
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብር 649.65ሚሊዮን አተረፈ
በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በማኑፋክቸሪነግ ዘርፍ የተሰማሩ አምስት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 174 ሚሊዮን አተረፉ
በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በንግድና አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ አራት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 77.6ሚሊዮን አተረፉ
በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ብር 52.3 ቢሊዮን አተረፉ
Back

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2012 በጀት ዓመት ብር 122.14 ቢሊዮን ገቢ አገኘ::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2012 በጀት ዓመት በዐለም አቀፍና በሀገር ውስጥ ትራንስፖርት መንገደኞችንና ዕቃዎችን በማጓጓዝ፣ የኤርፖርት አገልግሎትና ሆቴል መስተንግዶ በማቅረብ ፣ የጥገና አገልግሎትና የአቬሽን ስልጠና በመስጠት ፣ብር 149.72 ቢሊዮን ገቢ ለማግኘት አቅዶ ብር 122.14 ቢሊዮን ወይም የዕቅዱን  82 በመቶማግኘትችሏል፡፡

ይህ አፈጻጸም የታወቀው የአየር መንገዱ የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ መስከረም 18 ቀን 2013 .. በተገመገመበት ወቅት ነው፡፡ ግምገማ መድረኩን የመሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረመስቀል ሲሆኑ፣ የአየር መንገዱ ሥራአስፈጻሚዎች ፣ የኤጀንሲው የትራንስፖርት ዘርፍ ዳይሬክተርና ባለሙያዎች በግምገማው ተሳትፈዋል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውና የአቬሽንን ኢንዱስትሪ በከፍተኛ ሁኔታ የጎዳውን የኮቪድ-19 ተጽዕኖ አየር መንገዱ ተቋቁሞ ይህን ያህል ገቢ ሊያገኝ የቻለው በወረርሽኙ የተነሳ የመንገደኞች ቁጥር በከፍተኛ መጠን ሲቀንስበት የሕዝብ ማመላለሻ አውሮፕላኖቹን ወደጭነት ማጓጓዣ(ካርጎ) ፈጥኖ በመቀየር በወሰደው እርምጃ እንደሆነ በግምገማው ወቅት ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ የወጪ ቅነሳ ስልቶችን በጥናት ላይ ተመርኩዞ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በዚህም ከብር 5 ቢሊዮን በላይ ወጪ ሊያድን ችሏል፡፡ በቀጣይም ሠራተኞቹን ባሳተፈ መልክ ተጨማሪ ገቢ ሊያስገኙና ወጪ ሊቀንሱ የሚችሉ ተግባራትን በየጊዜው እያጠና እንደሚተገብር ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ካሉ 14 ሽህ ሠራተኞች 34 በመቶ ያህሉ ሴቶች ሲሆኑ ፣አብዛኞቹም በማኔጅመንት ፣በአብራሪነት እና ቴክኒሻንነ ትባሉ ከፍተኛ ኃላፊነትና ተከፋይ በሆኑ የሥራ መደቦች ላይ የሚሠሩ ናቸው፡፡ ይህ ሁኔታ ድርጅቱ ለሴቶች ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራ መሆኑን ያሳያል፡፡

በግምገማው መጨረሻ የኤጀንሲው ዋናዳይሬክተር አቶበየነገብረመስቀል አየር መንገዱ የወቅቱ ወርወሽኝ የፈጠረውን የገበያ መቀዛቀዝ የተለያዩ አማራጭ ገቢ ምንጮችንና የወጪ መቀነሻ ስልቶችን አጥንቶ ተግባራዊ ማድረጉ ለጥሩ ውጤት እንዳበቃው ገልጸዋል፡፡ በቀጣዩ የበጀት ዓመትም ይህንኑ ጥረቱን አጠናክሮ እዲቀጥል አስገንዝበዋል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎንም ገቢዎች በተቻለ መጠን በውጭ ምንዛሪ እንዲሆኑና በአንጻሩ የውጭ ምንዛሪ ወጪዎች ደግሞ ሊቀንሱ የሚችሉበት አማራጮች እንዲታዩ ፣ በጅምር ያሉ ፕሮጀክቶች ሊዘገዩ የሚችሉና ቶሎ መጠናቀቅ ያለባቸው ተለይተው ቅድሚያ የሚሰጣቸው ያለተጨማሪ ወጪ ተፋጥነው እንዲጠናቀቁ ጥረት እንዲደረግ ፣ካለው የገበያ መቀዛቀዝ አንጻር የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር (cash management) ጥንቃቄ የተመላበት እንዲሆን ፣እንዲሁም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጽዕኖ የአንድወቅት ብቻ ሳይሆን በዓለም ኢኮኖሚ ትስስር ላይ ቀጣይነት ያለው ለውጥ ሊያስከትል ስለሚችልበ ጥናት ላይ የተመሠረተ ዕቅድ አስቀምጦ መንቀሳቀስ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠው ግምገማው ተጠናቋል፡፡


  ክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል

 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

Web Content Display Web Content Display

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል መልዕክት

 

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 1097/2011  መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን እንደገና እንዲዋቀሩ ማድረጉን ተከትሎ በደንብ ቁጥር 445/2011 ተቋቁሟል፡፡ ኤጀንሲው ከቀድሞው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በተለየ መልኩ አዲስ ተልዕኮ ፣ የትኩረት መስክ እና አደረጃጀት እንዲይዝ ተደርጓል፡፡ 

አዲሱን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት ተከትሎ የተቋቋመውን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲን  በዋና ዳይሬክተርነት እንድመራ ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቶኛል፡፡ ኤጀንሲው በሥሩ 22 ተጠሪ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አሉት፡፡

ኤጀንሲው  የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውጤታማ ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና የኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓት ዝርጋታ ፣ አመራርና አስተዳደር ክትትል ፣በመንግሥት የልማት ድርጅቶችና አክሲዮን ማህበራት ውስጥ መንግሥት ያለውን የባለቤትነት መብት ማስጠበቅ ፣በመንግሥት ልማት ፖሊሲ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስምሪት መካከል የሚኖረውን ቅንጅት ማሳለጥ እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር  የመንግሥት የባለቤትነት ፣ የተቆጣጣሪ እና ፖሊሲ አውጪውን አካላት ኃላፊነትና ሚና በለየ መልኩ መተግበሩን ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ ዋና ዋና ዓላማዎችን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ሌሎች ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶችም በመቋቋሚያ ደንቡ ተገልፀዋል፡፡

ኤጀንሲው እነዚህን ዓላማዎች እና  ኃላፊነቶች ለማሳካትም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መልኩ ትርፋማነት ላይ አተኩረው እንዲሰሩ በማስቻል በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ማድረግ እና የሀገርን ኢኮኖሚ መደገፍ እንዲችሉ ማብቃት ይጠበቅበታል፡፡

የኤጀንሲው ፣ የተጠሪ የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ፈጻሚዎች ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት  ለመወጣት የመላው የሀገራችን ህዝብ እና የደንበኛና የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ድጋፍ ወሳኝ እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን፡፡

በመሆኑም በምንከተለው ግልጽ አሰራር መሰረት የደንበኛና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ድጋፍ እንደምናበረታታ እያስታወቅን፣ ለጋራ ዓላማችን ስኬት ለምታደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ክብር እንዳለን እና ትኩረት ሰጥተን ሁልጊዜም ለመሻሻል እንደምንሰራ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

Web Content Display Web Content Display