The Ministry of Finance (MOF) and the Public Enterprises Holding and Administration Agency (PEHAA) are pleased to announce the completion of a key milestone in partial privatisation of Ethio Telecom.
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከታክስ በፊት ብር 1.22 ቢሊዮን አተረፈ
የኢትዮ-ቴሌኮም በ2013 መጀመሪያው አጋማሽ ዓመት ከታክስ በፊት ብር 14.58 ቢሊዮን አስመዘገበ

Web Content Display Web Content Display

 

 

Press release

 

 

The Ministry of Finance (MOF) and the Public Enterprises Holding and Administration Agency (PEHAA) are pleased to announce the completion of a key milestone in partial privatisation of Ethio Telecom. Following the announcement of the privatisation process that started in 2018, the Government of Ethiopia is now ready to release an Expression of Interest (EOI) for the sale of a 40% stake in Ethio Telecom.

This is in line with the appointment of Deloitte as a lead transaction advisor, who is now on the final stage of completing the preparatory work which includes business plan, financial, legal and tax due diligence and business valuation following global best practice.

The issuance of the EOI on 15 June 2021 will allow international investors to express interest in acquiring a stake in Ethio Telecom, one of the largest telecom operators in Africa. Investors will be given 30 days to respond with an expression of interest. After the issuance of the EOI, the process will follow with a Request for Proposal (RFP); and the timeline for the release of the RFP will be communicated in due course, with the aim of completing the transaction in an efficient and streamlined manner.

Back

የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በመጀመሪያው አጋማሽ ዓመት ብር 60.4 ሚሊዮን ትርፍ ከታክስ በፊት አተረፈ

 

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ሥር ከሚገኙ እና በግብርና እና አግሮኢንዱስትሪ ዘርፍ ከተሰማሩ ልማት  ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የካቲት 3 ቀን 2013 ዓ.ም በኤጀንሲው አዳራሽ በተካሔደ ስብሰባ በ2013 የመጀመሪያው አጋማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙ ትርፍ ከታክስ በፊት ብር 60.4 ሚሊዮን ማግኘቱ ተገለጸ፡፡

ኮርፖሬሽኑ የግብርና ግብአቶችን እና የተሻሻሉ የእርሻ መሣሪያዎችን በማቅረብ ፣ የሜካናይዜሽን እና የቴክኒክ ሙያ ማሻሻያ የስልጠና አገልግሎቶችን በመስጠት ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን በአጋማሽ ዓመቱ ብር 1.017 ቢሊዮን ጠቅላላ ገቢ ለማግኘት አቅዶ ብር 1.48 ቢሊዮን ጠቅላላ ገቢ በማስመዝገብ የዕቅዱን 145 በመቶ ማሳካት ችሏል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ጠቅላላ ገቢ የብር 3.03 ሚሊዮን ኪሳራ ለማስመዝገብ ያቀደ ቢሆንም በመጀመሪያው አጋማሽ ዓመት የብር 60.4 ሚሊዮን ትርፍ ከታክስ በፊት ማስመዝገብ ችሏል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በተለይም የተፈጥሮ ምርት ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ በመሆኑ የተፈጥሮ ሙጫ ምርትን ለውጭ ገበያ በማቅረብ 508 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ማግኘት ችሏል፡፡

ከኮርፖሬሽኑ የሥራ ባህሪ አንጻር በመጀመሪያው የበጀት ዓመት አጋማሽ በቀጣይ ለሚገኝ ትርፍ ወጪ የሚደረግበትና ኪሳራ የሚያቅድበት ቢሆንም በአጋማሽ ዓመቱ በሀገሪቱ ተከሰተው የአንበጣ መንጋ የጎዳውን ሰብል በሽንብራ የመተካት ፍላጎት በመጨሩ፣ ስንዴን በመስኖ የማልማት ተግባራት በመጀመሩ እና እነዚህን ተከትሎ የምርጥ ዘር እና የማዳበሪያ ፍላጎት በመጨመሩ በተከናወነ ሽያጭ ምክንያት ትርፍ ሊያስመዘግብ ችሏል፡፡

ግምገማውን የመሩት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል ሲሆኑ ፣ የኤጀንሲውና የልማት ድርጅቶቹ ቦርድ እና ማኔጅምንት አባላትም ተሳትፈዋል፡፡ ግምገማው የድርጅቱን የኦፕሬሽን ፣የፋይናንስ ፣የፕሮጀክት፣ የሪፎርም እና የኮርፖሬት አስተዳደር ሥራዎች ግብ አፈፃፀም እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫን መሰረት አድርጎ የተካሔደ ነበር፡፡

ውጤቱ ተገኘው በቦርዱ በማኔጅመንቱ እና በሠራተኛው ብርቱ ጥረት እንደሆነ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ገልጸው እና ምስጋናቸውን አቅርበው፣ በቀጣዮቹ በጀት ዓመቱ ቀሪ ወራቶችም ይህንኑ ጥረታቸውን ይበልጥ አጠናክረው ኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ የያዛቸውን ግቦች እንዲያሳኩ አሳስበዋል፡፡


  ክቡር አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል

 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

Web Content Display Web Content Display

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የክቡር አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል  መልዕክት

በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 445/2011 ተቋቁሞ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው የመንግሥት  የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በስሩ በተለያዩ የኢኮኖሚ መስኮች የተሰማሩ 21 ተጠሪ የልማት ድርጅቶች አሉት፡፡

ኤጀንሲው እነዚህን ድርጅቶች ውጤታማ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና ፋይናንስ ሥርዓት የመዘርጋት፣ አመራርና አስተዳደራቸውን የመከታተል፣  በልማት ድርጅቶቹና አክሲዮን ማኅበራቱ ውስጥ መንግሥት ያለውን የባለቤትነት መብት የማስጠበቅ፣ በመንግሥት ልማት ፖሊሲ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስምሪት መካከል የሚኖረውን ቅንጅት የማሳለጥ እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን አስተዳደር  የመንግሥት የባለቤትነት፣ የተቆጣጣሪ እና የፖሊሲ አውጪውን አካላት ኃላፊነትና ሚና በለየ መልኩ መተግበሩን የማረጋገጥ ዋና ዋና ዓላማዎችንና ከእነዚሁ ጋር የተያያዙ  ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች እንዲያከናውን የተቋቋመ ነው፡፡

በመሆኑም ለኤጀንሲው የተሰጡትን ዓላማዎች እና  ኃላፊነቶች ለማሳካት ባለፉት ሁለት ዓመታት በለውጥ(Reform) ሥራዎችም ሆነ በኦፕሬሽን በርካታ ተግባራትን አቅዶ ፈጽሟል፡፡ አበረታች ውጤቶችንም አስመዝገቧል፡፡ በለውጥ ሥራ ረገድ ኤጀንሲውን ደረጃ በደረጃ ወደ የመንግሥት ይዞታ ኩባንያ (Government Holding Company) ለማሸጋገር ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመዳሰስ ባዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ላይ የአሠራር ሥርዓቶችንና የውስጥ አቅምን ለመገንባት ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቷል፡፡ በዚሁ መሠረት የፖርትፎሊዮ ሥራ አመራር፣የልማት ድርጅቶች ሥራ አመራር፣ የኤጀንሲ ተቋማዊ ሥራ አመራር፣ አስቻይ ሁኔታዎች እና አስተዳደር የሚሉ ዋና ዋና ተግባራት (Work streams) እና 16 እርምጃዎችን(Initiatives) ለይቶ ሠፊ ሥራ አከናውኗል፤ እያከናወነም ይገኛል፡፡

ከተከናወኑ ተግባራት መካከል በልዩ ልዩ ርዕሶች ለኤጀንሲውና ለልማት ድርጅቶች አመራሮችና ሠራተኞች ሥልጠናዎች መሰጠታቸው፣ የኮርፖሬት አስተዳደርና ፋይናንስ ሥርዓትን የተመለከቱ የተለያዩ መመሪያዎች ተዘጋጅተው ሥራ ላይ እንዲዉሉ መደረጉ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በኦፕሬሽንም  ረገድ የልማት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መልኩ ትርፋማነት፣ ተወዳዳሪነት እና ወጪ ቆጣቢነት ላይ አተኩረው እንዲሰሩ ለማስቻል በተደረገው ጥረት አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል፡፡

እኔ ኤጀንሲውን በዋና ዳይሬክተርነት  እንድመራ ከፍተኛ ኃላፊነት የተሰጠኝ እነዚህ በባለፉት ዓመታት የተጀመሩ የጋራ ጥረቶቻችንንና የተገኙ ውጤቶቻችንን  ይበልጥ በማጠናከርና የልማት ድርጅቶች በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ሆነው የሀገርን ኢኮኖሚ መደገፍ እንዲችሉ ለማብቃት ነው፡፡

ስለዚህ የኤጀንሲውና የተጠሪ የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ሠራተኞች ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት  ለመወጣት በየፊናችን እያደረግን ያለነው ርብርብ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ከዚህ አኳያ የመላው የሀገራችን ህዝብ እና የደንበኛና የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ተሳትፎና ድጋፍም ወሳኝ እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን፡፡ ለጋራ ዓላማችንም ስኬት ሁላችሁም ለምታደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ክብር እንዳለን እና ለመሻሻል ሁል ጊዜም ትኩረት ሰጥተን  እንደምንሰራ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡