በግብርና እና አግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ሁለት ኮርፖሬሽኖች የግማሽ በጀት ዓመት አፈጻጸም ተገመገመ
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብር 649.65 ሚሊዮን አተረፈ
በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በማኑፋክቸሪነግ ዘርፍ የተሰማሩ አምስት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 174 ሚሊዮን አተረፉ
በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በንግድና አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ አራት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 77.6 ሚሊዮን አተረፉ
በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ብር 52.3 ቢሊዮን አተረፉ
Back

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከታክስ በፊት 8.9 ቢሊዮን ብር አተረፈየኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2011 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ብር 8.9 ቢሊዮን አተረፈ፡፡ ድርጅቱ ይህን ትርፍ ሊያገኝ የቻለው መንገደኞችንና ዕቃ በአየር ወደ ተለያዩ የዓለማችን አገሮች በማጓጓዝ እና ሌሎች ተጓዳኝ አገልግሎቶችን በመስጠት ብር 114.6 ቢሊዮን ገቢ በማግኘቱ እንደሆነ የበጀት ዓመቱ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም. በተገመገመበት ወቅት ተገልጿል፡፡ ከአጠቃላይ ገቢው ውስጥ በውጭ ምንዛሪ የተገኘው 3.9 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መሆኑም በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

የዕቅድ አፈጻጸሙን ግምገማ የመሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገ/መስቀል ሲሆኑ፣የድርጅቱ የስትራቴጂክ ፕላኒንግና ትብብር ም/ፕሬዚዳንት አቶ ቡሴራ አወል፣ ሌሎች የማኔጅመንት አባላትና የኤጀንሲው የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዳይሬክተር ተገኝተዋል፡፡
በዕለቱ የድርጅቱ የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅትም የታየ ሲሆን፣ በዚህም ወቅት የአየር መንገድ ግሩፕ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ብር 155 ቢሊዮን ገቢ በማግኘት ብር 19 ቢሊዮን ከታክስ በፊት ለማትረፍ ማቀዱ ታውቋል፡፡

በግምገማው ማጠቃለያ ላይ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረመስቀል ድርጅቱ በ2011 ዕቅድ ዘመኑ የገጠመውን የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ተቋቁሞ ያስመዘገበው ውጤት የሚያስመሰግነው እንደሆነ ገልጸው፣በ2012 በጀት ዓመት ዕቅዱም ለማሳካት የየያዛቸው ግቦች የድርጅቱን ቀጣይ ዕድገት የሚያሳዩ ናቸው በማለት ለስኬታቸው አመራሩና መላው ሠራተኛ ጠንክሮ እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡


  ክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል

 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

Web Content Display Web Content Display

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል መልዕክት

 

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 1097/2011  መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን እንደገና እንዲዋቀሩ ማድረጉን ተከትሎ በደንብ ቁጥር 445/2011 ተቋቁሟል፡፡ ኤጀንሲው ከቀድሞው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በተለየ መልኩ አዲስ ተልዕኮ ፣ የትኩረት መስክ እና አደረጃጀት እንዲይዝ ተደርጓል፡፡ 

አዲሱን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት ተከትሎ የተቋቋመውን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲን  በዋና ዳይሬክተርነት እንድመራ ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቶኛል፡፡ ኤጀንሲው በሥሩ 22 ተጠሪ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አሉት፡፡

ኤጀንሲው  የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውጤታማ ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና የኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓት ዝርጋታ ፣ አመራርና አስተዳደር ክትትል ፣በመንግሥት የልማት ድርጅቶችና አክሲዮን ማህበራት ውስጥ መንግሥት ያለውን የባለቤትነት መብት ማስጠበቅ ፣በመንግሥት ልማት ፖሊሲ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስምሪት መካከል የሚኖረውን ቅንጅት ማሳለጥ እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር  የመንግሥት የባለቤትነት ፣ የተቆጣጣሪ እና ፖሊሲ አውጪውን አካላት ኃላፊነትና ሚና በለየ መልኩ መተግበሩን ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ ዋና ዋና ዓላማዎችን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ሌሎች ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶችም በመቋቋሚያ ደንቡ ተገልፀዋል፡፡

ኤጀንሲው እነዚህን ዓላማዎች እና  ኃላፊነቶች ለማሳካትም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መልኩ ትርፋማነት ላይ አተኩረው እንዲሰሩ በማስቻል በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ማድረግ እና የሀገርን ኢኮኖሚ መደገፍ እንዲችሉ ማብቃት ይጠበቅበታል፡፡

የኤጀንሲው ፣ የተጠሪ የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ፈጻሚዎች ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት  ለመወጣት የመላው የሀገራችን ህዝብ እና የደንበኛና የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ድጋፍ ወሳኝ እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን፡፡

በመሆኑም በምንከተለው ግልጽ አሰራር መሰረት የደንበኛና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ድጋፍ እንደምናበረታታ እያስታወቅን፣ ለጋራ ዓላማችን ስኬት ለምታደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ክብር እንዳለን እና ትኩረት ሰጥተን ሁልጊዜም ለመሻሻል እንደምንሰራ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

Web Content Display Web Content Display