Web Content Display Web Content Display

    ስኳር ኮርፖሬሽን 

ምስረታ      የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ጥቅምት 2003ዓ.ም ተቋቋመ 

ራዕይ: -  ቀጣይነት ባለው እድገት በ2016ዓ.ም በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች ሀገራት ተርታ መሰለፍ፣                    

ተልዕኮ: -  በሀገሪቱ ያለውን እምቅ ሃብት ለማልማት የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂና የሰው ሀይል አቅም በማፍራት ስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች በማምረትና የስኳር ተረፈ ምርትን ጥቅም ላይ በማዋል የሀገር ውስጥ ፍላጎት ከማርካትና የህዝቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ በተጨማሪ የጎላ የኤክስፖርት ድርሻ በመያዝ የሀገሪቱን ልማት መደገፍ፡፡                 

ኮርፖሬሽኑ ጥቅምት 2003ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን፣ ከመጋቢት 2008ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው  የዋና መስሪያ ቤት  የአደረጃጀት ለውጥ የተቋሙን ወሳኝ የስራ ሂደቶች መሠረት በማድረግ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ስር በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች የሚመሩ የስትራተጂያዊ ድጋፍ፣ የኢንቨስትመንት ጥናትና ልማት፣ የኦፕሬሽንስ እና የማርኬቲንግ የሥራ ዘርፎች ተዋቅረዋል፡፡ በእነዚህ ስርም በሥራ አስፈጻሚዎች የሚመሩ 21 የሥራ ክፍሎች ተቋቁመዋል፡፡ እንዲሁም ለዋና ሥራ አስፈጻሚው በቀጥታ ተጠሪ የሆኑ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት፣ የፋይናንስ፣ የምርምርና ልማት ማዕከል፣ የፕላኒንግ፣ የማሽነሪና የቴክኒክ አገልግሎት፣ የሥነ ምግባርና የመልካም አስተዳደር እና የኦዲት የሥራ ክፍሎች በአዲስ መልክ ተደራጅተዋል፡፡

በተጨማሪም የዋና ሥራ አስፈጻሚ የኮርፖሬት ሪፎርምና አቅም ግንባታ እና የፕሮጀክትና ኦፕሬሽንስ አማካሪዎች በመዋቅሩ ውስጥ ተካተዋል፡፡

የሰው ሐይል

ወንድ : - 467, ሴት : - 155  ,ድምር : - 622

የተቋቋመበት አላማ : -

 • የሸንኮራ አገዳና ስኳር የሚያስገኙ ሌሎች ሰብሎች ማልማት፣
 • ስኳር፣ የስኳር ውጤቶችን፣ የስኳር ተረፈ ምርቶችን እና የስኳር ተረፈ ምርት ውጤቶችን በፋብሪካ ማዘጋጀትና ማምረት፣
 • ምርቶቹንና ተረፈ ምርቶቹን ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣
 • አዳዲስና የማስፋፊያ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት፣ የዲዛይን ዝግጅት፣ የቴክኖሎጂ መረጣና ድርድር፣ የተከላና ኮሚሽኒንግ ሥራዎች እንዲካሄዱ ማድረግ፣
 • ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በሸንኮራ አገዳና በስኳር አመራረት ቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር ማካሄድና ጠቃሚ ውጤቶችን በስራ ላይ ማዋል፣
 • አቅሙ ካላቸው የሀገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች የሚያስፈልጉ የማምረቻ መሳሪያዎችና መለዋወጫዎች ዲዛይንና ፋብሪኬሽን ሥራዎች በሀገር ውስጥ እንዲከናወኑ ማድረግ፣
 • በሕግ መሰረት ለስራው የሚያስፈልገው መሬት ባለይዞታ መሆንና ማልማት፣
 • የአገዳ ምርታቸውን ለመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች የሚያቀርቡ አገዳ አብቃዮችን ማበረታታትና መደገፍ፣
 • ለስኳር ኢንዱስትሪ የሚፈለገውን የሰለጠነ የሰው ሃይል በሚፈለገው አይነት፣ መጠንና ጥራት ለማፍራት እንዲቻል ከሚመለከታቸው የትምህርት ተቋማት ጋር መተባበር፣
 • የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የሚያወጣውን መመሪያና የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ቦንድ መሸጥና በዋስትና ማስያዝ እና ከሀገር ውስጥና ከውጭ የገንዘብ ምንጮች ጋር የብድር ውል መደራደርና መፈራረም፣
 • አላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን መስራት ናቸው፡፡

አድራሻ:  ካዛንቺስ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አካባቢ

ስ.ቁ.  251 11 552 66 53/52 68 96

ፖስታ ሳ.ቁ. - 20034 ኮድ 1000

አዲስ አበባ  

ድረ-ገጽ አድራሻ : -  www.etsugar.gov.et